=<({አል-ኢኽላስ 112:1-4})>=
ﺑﺴﻢ ﺍﻟﻠﻪ ﺍﻟﺮﺣﻤﻦ ﺍﻟﺮﺣﻴﻢ
1. በል! እርሱ አላህ አንድ ነው።
2. አላህ (የሁሉ) መጠጊያ ነው።
3. አልወለደም፤ አልተወለደምም።
4. ለእርሱም አንድም ብጤ የለውም።
![]() =<({አል-ቁርአን 96:1-5})>=
![]() በቡኻሪ በተዘገበው ሐዲስ መሰረት እውቀትን መሻት በእያንዳንዱ ሙስሊም ላይ ግዴታ ነው። ![]() |
---|
እናት አለም ክብሬ እማየ አንደቤቴ፤
የመኖሬ ዋስትና የዘጠኝ ወር ቤቴ፤
በደምሽ ታንፃ መልካሟ ሂወቴ፤
እኔ ስስቅ ስቀሽ ስከፋ ተከፍተሽ፤
ሲርበኝ ተርበሽ
ሲጠማኝ ተጠምተሽ፤
በመልካሙ ምኞት መልካሙን አስበሽ፤
የወደፊት ተስፋየን ሂወቴን አብርተሽ፤
ለፍተሽ ጥረሽ ግረሽ ደክመሽ አስተምረሽ፤
ስሳሳትም መክረሽ ሃሳቤን ቀይረሽ፤
ትክክለኛውን መንገድ መስመሩን አስይዘሽ፤
በርካታ ቢሆንም እማየ ውለታሽ፤
ውለታሽን ከፋይ ልሆን ቃል ስገባልሽ፤
የሂጠወቴ ብርሃን እማየ እንዳይከፋሽ፤
የትላንቱ ህፃን ዛሬ ሰው ሁኛለሁ፤
ክፉና በጐውን ማስታወስ ችያለሁ፤
እናታ አለም ክብሬ ሁሌም እወድሻለሁ!!!
=<({አል-ቁርአን 17:23-34})>=
{23} ጌታችሁም ከእሱ በቀር ያለን ነገር እንዳታመልኩ እና ለቤተሰቦቻችሁ ቅን ትሆኑ ዘንድ ደነገገ። በአንተ ዘንድ ኾነው አንዳቸው ወይም ሁለታቸው የእርጅና እድሜ በደረሱ ጊዜ ኡፉ አትበላቸው፤ አትገላምጣቸውም። መልካምን ቃል ተናገራቸው።
{24} ለእነሱ የሽንፈትና የውርደት ክንፍህን በእዝነት ዝቅ አድርግላቸው። እናም «ጌታዬ ሆይ! በሕፃንነቴ (በርኅራኄ) እንዳሳደጉኝ ሁሉ ምህረትህን ስጣቸው» በል።
እማ
:¨·.·¨:
`·.. እናት አለም ክብሬ ሁሌም እወድሻለሁ!!!
የወጣቱ ተልዕኮ አድራሻ
ኢስላማዊ መጽሐፎችን ያውርዱ |
---|